የ2016 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በስቶክሆልም ከተማ በድምቀት ተከበረ !

(መስከረም 17 ቀን 2016 ዓ.ም ስቶክሆልም ፣ ስዊድን )

የ2016 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የስዊድን፣ ስካንድናቭያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በስቶክሆልም ስዊድን በድምቀት ተከብሯል።

በዕለቱ ነገረ መስቀሉን የተመለከተ ሰፊ ትምህርተ ወንጌል በመጋቤ ሐዲስ ነቅዐ ጥበብ ከመሰጠቱ በተጨማሪ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እና በስቶክሆልም ከተማ የሚገኙት አራቱም አድባራት ሰ/ት/ቤት ወጣቶች ያሬዳዊ ዝማሬ ቀርቧል፣ መንፈሳዊ ትርዒቶችም ታይተዋል።

በመጨረሻም በብፁዕ አቡነ ኤልያስ የስዊድን፣ ስካንድናቭያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ከተሰጠ በኃላ በብፁዕነታቸውና ደመራው ተለኩሷል ።

በደመራው በዓል ላይ ከሀገር ቤት በእንግድነት የተገኙትን መጋቤ ሐዲስ ነቅዐ ጥበብን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ የሰ/ት/ቤት አባላትና የከተማው በርካታ ምእመናን ተገኝተዋል።