የ፳፻፲፮ ዓ.ም የጥምቀት በዓል ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከበረ !

(ጥር ፲፩ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም ስቶክሆልም ፣ ስዊድን )

የ፳፻፲፮ ዓ.ም የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በብፁዕ አቡነ ኤልያስ የስዊድን፣ ስካንድናቭያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መልካም ፈቃድ:
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የጣሊያንና አካባቢው ሀገረ ስብከት  ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በስዊድን ስቶክሆልም  በድምቀት ተከብሯል።
በዓሉ ከዋዜማው ጀምሮ ዐራቱም አድባራት ማለትም

  • ደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም መንበረ ጵጵስና፣
  • መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ፣
  • ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖትና
  • የቬስትሮስ ቅዱስ አማኑኤል

አብያተ ክርስቲያናት ከየቤተ መቅደሶቻቸው ተነስተው  በዓለ ጥምቀቱን ለማክበር ወደ ተዘጋጀው ልዩ ቦታ በመውረድ  የበዓለ ጥምቀቱ ዋዜማ ከተራው በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል ።
ሌሊቱን በሙሉ ሊቃውንቱ  በማኅሌት፣ ምዕመናን በዝማሬና በእልልታ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ያደሩ ሲሆን በመቀጠልም
በብፁዕነታቸው መሪነት ሥርዓተ ቅዳሴው ከተጠናቀቀ በኋላ  በዓሉን በተመለከተ ትምህርተ ወንጌልና  ቃለ ምዕዳን
ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ባሕረ ጥምቀቱ ተባርኮ ሕዝቡ ጠበል ከተረጨ በኋላ ታቦታተ ሕጉ ወደየመንበረ ክብራቸው በሰላም ተመልሰዋ።

በበዓሉ ላይ የሀገረ ስብከታችን የሥራ ሐላፊዎች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፣የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች፣ የሁሉም አድባራት ካህናትና ዲያቆናት፣የሰንበት ት/ቤት መዘምራንና በርካታ ምዕመናን ተግኝተዋል።

የሀገረ ስብከቱ ሚዲያ ክፍል