የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዕረፍት በዓል ብፁዕ አቡነ ኤልያስ በተገኙበት በስዊድን ስቶክሆልም ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ተከበረ !

የብፁዕ አባታችን የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዕረፍት በዓል ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የስዊድን፣ ስካንዲናቭያንና የግሪክ ሀገሮች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በተገኙበት በስዊድን ስቶክሆልም ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን መጋቢት 01 ቀን 2016 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።

በዓሉ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ዲያቆናትና ምእመናን በተገኙበት በማኅሌት፣ በቅዳሴና በስብከተ ወንጌል በድምቀት ተከብሮ ውሏል::