የአህጉረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ

ብጹእ አቡነ ኤልያስ የስዊድንና የአካባቢ ሐገሮች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ናቸው።
ብጹእ አባታችን የሀገረ ስብከቱ የበላይ ኃላፊ እንደመሆናቸው መጠን፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት የሚከተሉትን ተግበራት በበላይነት እንዲያከናውኑ ከቅዱስ ሲኖዶስ ታላቅ ኃላፊነት ተሰጥቶአቸዋል። ብጹእነታቸውም በታላቅ ብርታት እያከናወኑ ይገኛሉ፣ ወደፊትም ያከናውናሉ፡-

  1. የሀገረ ስብከቱ ጽቤትና ጠቅላላ የቤተ ክህነት አስተዳደር የበላይ ኃላፊ፣ እንዲሁም የጠቅላላው ሰበካ መንፈሳዊ ጉበኤ ርእሰ መንበር ናቸው።
  2. በሀገረ ስብከታቸው ለምትገኘው ለጠቅላላዋ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አባት እንደመሆናቸው መጠን፣ ለሰበካ ጉበኤያት መሪዎች በየጊዜው መንፈሳዊ ምክር፣ መመሪያና ቡራኬ ይሰጣሉ፣ ያበረታታሉ። ለካህናት፣ ለምእመናን፣ ለሰንበት ትቤት ህፃናትና ወጣቶች ትምህርት ይሰጣሉ፣ ያጽናናሉ።
  3. አንዲትና ቅድስት፣ ከሁሉ በላይና ሐዋርያዊት የሆነችው ቤተ ክርስቲያናችን ጥንታዊነትዋና ታሪካዊነትዋ በሰላም ተጠብቆ እንዲኖር፣ እንዲሁም ተከታዮችዋ ምእመናን በባእድ ሃይማኖት አስፋፊዎች እንዳይሰረቁ ብርቱ ጥበቃ ያደርጋሉ።
  4. በፍትህ መንፈሳዊ አንቀጽ 6 እና 7 በተደነገገው መሠረትና በቃለ አዋዲው አንቀጽ 20 ንኡስ አንቀጽ 8 እና 9 የተመለከተውን መስፈርት አሙዋልተው ለቀረቡት የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች፣ በቃልና በጽሁፍ ፈተና እየተጣራ ፈተናውን ላለፉት ብቻ የዲቁናና የቅስና ማእረግ ይሰጣሉ። ማእረጉን ለተቀበሉትም የምስክር ወረቀት እንዲሰጣቸው ያደርጋሉ።
  5. ከሚያገለግሉበት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መሸኛ ደብዳቤ ላልያዙ በቂ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ለሌላቸው ክህነት አይሰጡም።
  6. በሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ እያስጠኑና እያስወሰኑ ለሀገረ ስብከቱ የሚያስፈልጉትን ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎች እንዲቁዋቁዋሙና ኃላፊዎችም እንዲመደቡ ያደርጋሉ። አፈጻጸሙን ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ያሳውቃሉ።
  7. በሀገረ ስብከቱ ክልል ውስጥ አዲስ ለሚከተሉት አብያተ ክርስቲያናት በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ፈቃድ ይሰጣሉ። የመሠረት ድንጋይ ያኖራሉ። ቅዳሴ ቤቱን ይባርካሉ።
  8. በሀገረ ስብከቱ ክልል ውስጥ በመጀመሪያ ደረጃ ሆነ በይግባኝ የሚቀርበውን የሕግና ሥነ ሥርዓት ጉዳይ በሀገረ ስብከቱ ጽቤት እንዲታይ ያደርጋሉ። ይግባኝ የሚጠየቅበትም ጉዳይም ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ወይም ለቅዱስ ሲኖዶስ እንዲተላለፍ ያደርጋሉ።

እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን ይባርክ